ኢትዮ ቴሌኮም የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

ጥቅምት 02/2014 (ዋልታ) ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ሪጅንና የአምቦ ከተማ ወጣቶች ህብረት ለ5 ሺህ 418 ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ አበረከቱ።

ተማሪዎቹ አነስተኛ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦች አባላት መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ሪጅን በዲላ ከተማ ለ600 ተማሪዎች ደብተሮችን ሲያስረክብ በሪጅኑ የኦፕሬሽን ዳይሬክተር ጁነዲን አብዱልቃድር በትምህርት መሳሪያዎች ችግር ምክንያት ተማሪዎች ከትምህርት ውጪ እንዳይሆኑ ድጋፍ እየተደረገ ነው ብለዋል።

ሪጅኑ ከ1 ነጥ 5 ሚሊዮን ብር በላይ በማውጣት በተለያዩ ከተሞች ከሚገኙ 32 ትምህርት ቤቶች ለተወጣጡ ለ4 ሺህ 418 ልጆች የደብተር ድጋፍ አድርጓል።

በዲላ ከተማ ከአምስት ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ 600 ተማሪዎች የተደረገው ድጋፍ የዚሁ አካል መሆኑን አስታውቀዋል።