ኢትዮ ቴሌኮም የ 3 ዓመት ስትራቴጂን ከሐምሌ ጀምሮ ተግባራዊ ማድረጉን ገለጸ

ፍሬህይወት ታምሩ

መስከረም 16/2015 (ዋልታ) ኢትዮ ቴሌኮም አዲስ መሪ የተሰኘ የ3 ዓመት ስትራቴጂ ከሐምሌ ጀምሮ ተግባራዊ ማድረጉን ገለጸ።

የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ባለፉት 3 ዓመታት ድልድይ የተሰኘ ስትራቴጂ ይፋ ተደርጎ ወደ ስራ መገባቱን አስታውሰው በዚህም የስትራቴጂ ዘመን ኩባንያው በደንበኞች ብዛት የ75.6% እድገት በገቢ የ76% እድገት ማስመዝገቡን ገልጸዋል።

በውጭ ምንዛሬ ገቢ የ104% እድገትና የተጣራ ትርፍ 142% እድገት እንዲሁም በስማርት ቀፎ ብዛት 125% እድገት አስመዝግቧልም ነው ያሉት።

86% የታሪፍ ቅናሽ በማድረግ 306 ምርትና አገልግሎቶች 140 አዳዲስ እና 166 ነባር የሀገር ውስጥና የዓለም አቀፉ ምርትና አገልግሎቶች አቅርቧል ብለዋል።

የሰሜኑ የሀገሪቱ ጦርነት እና ኮቪድን እንደ ችግር በማንሳት ይህንንም በመቋቋም የተሻለ አፈጻጸም ማስመዝገብ ተችሏል ብለዋል።

የኩባንያው በአዲስ ጅማሮ በአዲስ እይታ ከኮሙዩኒኬሽን ባሻገር የዲጂታል እና የፋይናንስ አገልግሎቶችን ዙሪያ እድገት እንዲኖር የማስቻል ራዕይ የሰነቀ መሪ የተሰኘ የሦስት ዓመት የእድገት ስትራቴጂ ቀርጾ እ.ኤ.አ ከሐምሌ 01 ቀን 2022 ጀምሮ በተግባር ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።

መሪ ስትራቴጂ መሪ የዲጂታል አገልግሎትን የማሳደግ ራዕይ ይዞ አስተማማኝ የኮሙዩኒኬሽን አና የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት በማቅረብ የኢትዮጵያ ን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የማፋጠን ተልዕኮ አንግቦ ሰው ተኮር የሆነ አገልግሎት በታማኝነትና በልህቀት ማህበራዊ ኃላፊነትን በመወጣት በአብሮነት እንሰራለን ብለዋል።

በብርቱካን መልካሙ

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW