ኢንስቲትዩቱ በመጪው ክረምት መደበኛ እና ከመደበኛ በላይ ዝናብ ሊኖር እንደሚችል አስታወቀ

ግንቦት 8/2014 (ዋልታ) በመጪው የክረምት ወቅት ዋነኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የኢትዮጵያ አካባቢዎች ላይ መደበኛ እና ከመደበኛ በላይ ዝናብ ሊኖር እንደሚችል የኢትዮጵያ ሚቲዮሮሎጂ ኢንስቲትዩት ገልጿል።

እንደ ኢንስቲትዩቱ ትንበያው፣ በከረምቱ ምዕራብ፣ የደቡብ ምእራብ፣ የመካከለኛው እና የምሥራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች በአብዛኛው መደበኛውን ዝናብ ሲያገኙ፣ የሰሜናዊው አጋማሽ አካባቢዎች ደግሞ መደበኛ እና ከመደበኛ በላይ ዝናብ ሊያገኙ ይችላሉ።

በተጨማሪም በደቡብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከላሊና ክስተት ጋር በተያያዘ በወቅቱ መጨረሻ ወር ላይ ሊያገኙ በሚችሉት አነስተኛ መጠን ያለው ዝናብ ተፅዕኖ ውስጥ ሊገቡ እንደሚችልም ተገልጿል።

የአየር ትንበያውን መሠረት በማድረግ በዚህ ወቅት የሚካሄደውን የግብርና ሥራዎችን ከባለሙያዎች ጋር በመቀናጀት ማከወን እንደሚገባ መገለጹን የኢቢሲ ዘገባ አመላክቷል።

በሚኖረው ከባድ ዝናብ ሊከሰት የሚችለውን የጎርፍ እና ሌሎች ጉዳቶችን ለመቅረፍ ከወዲሁ ጥንቃቄ ማድረግ እንሚገባም የኢትዮጵያ ሚቲዮሮሎጂ ኢንስቲትዩት አሳስቧል።