ኢንስቲትዩቱ በ7 ሚሊየን ብር ወጪ ያስገነባውን አዲስ የምግብ ደህንነት ላቦራቶሪ አስመረቀ

ሚያዝያ 06/2013 (ዋልታ) – የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በሰባት ሚሊየን ብር ወጪ ያስገነባው እና  በዘመናዊ መልኩ የተሰራ የምግብ ደህንነትና የምግብ ማይክሮ ባዮሎጂ የምርምር ላቦራቶሪን አስመርቋል፡፡

ረጅም አመታት ሲሰራበት የቆየ ህንፃ በማርጀቱና ጠባብ በመሆኑ ለስራ አመቺ እና ከወቅቱና ከጊዜው ጋር የሚሄድ ባለመሆኑ አዲስና ዘመናዊ ላቦራቶሪ መገንባት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ በዘመናዊ መልክ መሰራቱ ተገልጿል፡፡

ላቦራቶሪው የውሃ ወለድ ወረርሽኝ፣ የችግሩ መነሻ ምክንያት ላይ ምርመራ እና ምግብና ውሃ ጥራት እና ደህንነት ላይ ምርመራ እንደሚያካሂድም በምረቃ ፕሮግራሙ ተጠቁሟል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳሬክተር ዶ/ር ኤባ አባተ መገኘታቸውን ከኢንስቲትዩቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡