ኢጋድ የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ፅኑ አቋም እንዳለው ገለጸ

ኅዳር 5/2015 (ዋልታ) የምስራቅ አፍሪካ ልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ፅኑ አቋም እንዳለው ገለጸ፡፡

የኢጋድ ዋና ጸሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) በጅቡቲ የሩሲያ አምባሳደር ጎሎቫኖብ ሚካሄሊ ጋር በቀጣናው የሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡

ዋና ጸሐፊው በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ እንዳስታወቁት ኢጋድ የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ፅኑ አቋም እንዳለው ለአምባሳደሩ አስረድተዋል፡፡

ዋና ጸሐፊው በሩሲያ አፍሪካ 2023 ጉባኤ ላይ እንዲሳተፉ በሩሲያ ፕሬዝዳንት ቨላድሚር ፑቲን ለቀረበላቸው ግብዣም ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW