ኤርትራ በውጭ አገራት የተደረጉትን የተቃውሞ ሰልፎች የመነሳሳትና የኩራት ምንጭ ስትል ገለፀች

ኅዳር 13/2014 (ዋልታ) በኢትዮጵያዊያና ኤርትራዊያን የተደረጉት የተቃውሞ ሰልፎች በእውነት የመነሳሳት እና የኩራት ምንጭ መሆናቸውን ኤርትራ አስታወቀች፡፡

የማስታወቂያ ሚኒስትሩ የማነ ገብረ መስቀል ‹‹የአፍሪካ ቀንድ ተናግሯል›› ሲሉ ስለሰሞነኛው ሰልፍ ጽፈዋል፡፡

አገራት አንድ በመሆን ጣልቃ የሚገቡ አገራትን በ#NoMore (በቃ) ንቅናቄ መቃወማቸው አስደሳች መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ኢትዮጵዊያን እና ኤርትራዊያን አንድ በመሆን ጣልቃ የሚገቡ አንዳንድ ምዕራባውያንን በማውገዝ የእራስ ፍላጎቶቻቸውን እና ምኞቶቻቸውን በጋራ ያሳካሉ ብለዋል፡፡