‘ኤችአር 6600’ እና ‘ኤስ 3199’ ረቂቅ ሕጎችን የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ በዋሺንግተን ዲሲ ተካሄደ

ሚያዝያ 10/2014 (ዋልታ) ‘ኤችአር 6600’ እና ‘ኤስ 3199’ ረቂቅ ሕጎችን የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ በአሜሪካ ዋሺንግተን ዲሲ ተካሄደ።
ኋይት ሃውስ ፊት ለፊት በተካሄደው ሰልፍ “ማዕቀብ ይገድላል”፣ ”ጸረ-ኢትዮጵያና ኤርትራ የሆኑትን ረቂቅ ሕጎች እንቃወማለን”፣ ”ኤችአር 6600’ እና ኤስ 3199’ ይሰረዙ” እና ”ፍላጎትን በኃይል ለመጫን የሚደረግ ማንኛውም ድርጊት እንቃወማለን አንቀበልም” የሚሉ መልዕክቶች መተላለፋቸውን የሰላምና አንድነት ለኢትዮጵያ ማኅበር የዋሺንግተን ግብረ ኃይል መረጃ አመልክቷል።
ሰልፈኞቹ ሕጎቹ በኢትዮጵያ ሰላምን ለማምጣት እየተደረገ ያለውን ጥረት እውቅና ያልሰጠና በሰላም ሂደቱ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ የሚያሳድር ነው ብለዋል።
ረቂቅ ሕጎችን በመቃወም በኋይት ሃውስ ፊት ለፊት የሚካሄደው ሰልፍ በቋሚነት በየሳምንቱ እንደሚከናወን ግብረ ኃይሉ ማሳወቁን ኢዜአ ዘግቧል።