‘ኤች አር 6600’ እና ‘ኤስ 3199’ ረቂቅ ሕጎችን የሚቃወም ሰልፍ ዛሬ በሎስ አንጀለስ ይካሄዳል

ሚያዝያ 3/2014 (ዋልታ) ‘ኤች አር 6600’ እና ‘ኤስ.3199’ ረቂቅ ሕጎችን የሚቃወም ሰልፍ ዛሬ በካሊፎርኒያ ግዛት ሎስ አንጀለስ ከተማ ይካሄዳል።
በሰልፉ ላይ ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን እንደሚሳተፉም ተጠቁሟል፡፡
በተያያዘ ዜና ‘ኤች አር 6600’ እና ‘ኤስ.3199’ ረቂቅ ሕጎችን የሚቃወም ሰልፍ ትናንት በዋሺንግተን ዲሲ ተካሂዷል።
በሰልፉ ‘ኤችአር 6600’ እና ‘ኤስ.3199’ ረቂቅ ሕጎች ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊያንን የሚጎዱ በመሆናቸው ሊሰረዙ ይገባል ተብሏል።
ሕጎቹ ለረጅም ጊዜ የቆየውን የኢትዮጵያና አሜሪካ ግንኙነት የሚጎዳ እንደሆነና የሁለቱ አገራት ጥቅም የማያስጠብቅ እንደሆነም ገልጸዋል።
በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ኢትዮጵያዊያን፣ ኤርትራዊያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች መሳተፋቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
‘ኤችአር 6600’ እና ‘ኤስ.3199’ ረቂቅ ሕጎችን የሚቃወም ሰልፍ በጣሊያን ሮም በቅዳሜ ዕለት መካሄዱም የሚታወስ ነው፡፡