ኤጀንሲው በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ታግደው የነበሩ አገልግሎቶችን መስጠት ሊጀምር ነው

                                                                    የአዲስ አበባ ከተማ ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ

የካቲት 10/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታግደው የነበሩ አገልግሎቶች ከየካቲት 14/2014 ዓ.ም ጀምሮ መስጠት እንደሚጀምር አስታውቋል፡፡

ኤጅንሲው ከዚህ ቀደም በአገር ዐቀፍ ደረጃ ከአዲስ የነዋሪነት መታወቂያ አገልግሎት ውጪ ታግደው የነበሩ አገልግሎቶች እንደሚጀመሩም ነው የገለጸው፡፡

በመሆኑም በሁሉም ክፍለ ከተማ በየወረዳው በተዘጋጀ መርሃ ግብር ነዋሪው መስተናገድ የሚችል መሆኑን የኤጀንሲው መረጃ ያመለክታል።

ሌብነትን በመፀየፍ ስጋት እየሆነ የመጣውን ሰነድ አስመስሎ በመስራት የሚደረግ ማጭበርበርን ማኅበረሰቡ እንዲከላከልም ኤጀንሲው ጥሪ አቅርቧል፡፡