ኤጀንሲው ከተለያዩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር በመሆን በአዳማ ከተማ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አከናወነ

ነሃሴ 14/2013 (ዋልታ) – የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ከተለያዩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር በመሆን በአዳማ ከተማ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አከናውኗል፡፡

በዚህ የሶስተኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ 400 የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችና የኤጀንሲው ሰራተኞች ተሳትፈዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ ለምግብነት የሚውሉ 5 ሺህ የፍራፍሬ ችግኞች በአዳማ ኦቦ ፓርክ ተተክለዋል፡፡

ዛሬ የተተከለው ችግኝ ለአፈር ጥበቃ እና ለምግብ ዋስትና የሚኖረው ፋይዳ ከፍተኛ ነውም ተብሏል፡፡

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ም/ል ዳይሬክተር ፋሲካው ሞላ ኢትዮጵያ ፈተና ውስጥ በምትገኝበትና ከየአቅጣጫው የተጋረጠባትን ጫና ለመመከት በምታደርገው ጥረት ጀግናውን የአገር መከላከያ ሰራዊት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በሎጂስቲክስና በገንዘብ መደገፍ ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በመጪው ማክሰኞ ለአገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍና የደም ልገሳ እንደሚያከናውኑ ተገልጿል፡፡

(በሳሙዔል ሃጎስ)