“እኔ የእህቴ ጠባቂ ነኝ” በሚል የሴቶች ቀን እየተከበረ ነው

የካቲት 27/2014 (ዋልታ) “እኔ የእህቴ ጠባቂ ነኝ” በሚል መሪ ሀሳብ የሴቶች ቀን በተለያዩ መርሃ ግብሮች እየተከበረ ይገኛል፡፡
በየዓመቱ ማርች  8 የሚከበረው የሴቶች ቀን በኢትዮጵያ ለ46ኛ ጊዜ ነው በመከበር ላይ የሚገኘው።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች፣ ህፃናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ሀና የሺንጉስ (ዶ/ር) ሴቶች መብታቸው እንዲከበር እና በማንኛውም አገራዊ ጉዳይ ላይ እኩል ተሳታፊ እንዲሆኑ የተለያዩ ሥራዎች መሰራቱን ተናግረዋል።
ባለፉት ዓመታትም የሴቶች ተሳትፎ በማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ እያደገ መምጣቱን ኃላፊዋ ገልፀዋል።
በመርሃ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
በሱራፌል መንግሥቴ
ለፈጣን መረጃዎች፦
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!