እንዲያውቁት

የዋልታ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬት ሕጋዊ የፌስቡክ ገጽ https://www.facebook.com/waltainfo ትናንት በገጠመው የቴክኒክ ችግር ምክንያት መረጃዎችን ማድረሱን ማቋረጡ ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጂ የተፈጠረውን የቴክኒክ ችግር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ በመሆን የፈታን ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ወደ መደበኛ የፌስቡክ ገጻችን መመለሳችንን በታላቅ አክብሮት ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡

በመሆኑም ለተፈጠረው የቴክኒክ ችግር ይቅርታ እየጠየቅን የገጠመንን ችግር ለመፍታት ለተባበራችሁን እንዲሁም ወደ ፌስቡክ ገጻችን እስክንመለስ በትዕግስት ለጠበቃችሁን ወዳጆቻችን በሙሉ ምስጋናችን የላቀ ነው፡፡

ዋልታ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬት