ኦሞ ኩራዝና ጊዳቦ መስኖ ፕሮጀክቶች ላይ ያተኮረ ውይይት እየተካሄደ ነው

ኅዳር 18/2014 (ዋልታ) በደቡብ፣ ሲዳማና ኦሮሚያ ክልሎች እየተገነቡ በሚገኙት የኦሞ ኩራዝና ጊዳቦ መስኖ ፕሮጀክቶች ላይ ያተኮረ ውይይት በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ነው።
በውይይቱ ላይ የግብርና ሚኒስትሩ ኡመር ሁሴን፣ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚንስትር አይሻ መሀመድ፣ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እርስቱ ይርዳው፣ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ እና ሌሎችም የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
ውይይቱ በሁለቱ የመስኖ ፕሮጀክቶች ውጤታማነት ላይ ያተኮረ መሆኑን ከደቡብ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።