ኦነግ ሸኔ ከህወሓት ጋር ህብረት መሰረተ

ነሃሴ 05/2013 (ዋልታ) – በኢፌዲሪ የህዝብ ተወካይ ምክር ቤት አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀው ኦነግ ሸኔ ከሽብርተኛው ህወሓት ጋር ህብረት መሰረተ፡፡

ጃል መሮ በመባልም የሚታወቀው የኦሮሞ ነፃነት ወታደር አልያም ሸኔ መሪ ኩምሳ ድሪባ  መንግሥትን በወታደራዊ ኃይል ለመገልበጥ ከጁንታው ጋር መቀላቀላቸውን ለአሶሺየትድ ፕሬስ በሰጡት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት አነግ ሸኔ ከህወሐት ተልኮ እንደሚቀበል ሲገልጽ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

በኢፌዲሪ የህዝብ ተወካይ ምክር ቤት አሸባሪ የተባሉት ሁለቱ ድርጅቶች ጥምረት መፍጠር መንግስት ሲያቀርብ የነበረውን ክስ የሚያጠናክር ሆኖ ተገኝቷል፡፡

መንግስት በትግራይ በወሰደው የህግ ማስከበር ዘመቻ ወቅት የሸኔ አባላት ከህወሀት ጋር እደተሰለፉ መገለጹ አይዘነጋም፡፡