ከማዕድን ዘርፍ በበጀት ዓመቱ 681 ሚሊየን ዶላር ገቢ ተገኘ

ነሃሴ 22/2013 (ዋልታ)- በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከማዕድን ዘርፍ 681 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ገለፀ።
ሚኒስቴሩ የ2013 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸሙንና የአዲሱን በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎቹን የተመለከተ መግለጫ ሰጥቷል።
በመግለጫው በዓመቱ የባህላዊ ወርቅ አምራቾች የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ችግር፣ የመሠረተ ልማት በሚፈለገው ደረጃ አለመሟላትና የፀጥታ ችግሮች እንደነበሩ ተነስቷል። ያም ሆኖ ከማዕድን ዘርፉ 681 ሚሊዮን ዶላር መገኘቱ ተገልጿል።
በሌላ ዜና የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ሠራተኞች መለገሳቸውን ኤዜአ ዘግቧል።