ዛሬ ከሳዑዲ አረቢያ የተመለሱ ዜጎች

ከሳዑዲ አረቢያ ተመላሽ ዜጎች

ጳጉሜ 1/2013 (ዋልታ) በተለያዩ ሀገራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ እየተደረገ ባለው ጥረት በዛሬው ዕለት ከሳዑዲ አረቢያ ጂዳ 84 ህጻናትን ጨምሮ 437 ዜጎቻችን ወደ አገራቸው መመለሳቸው ተገለጸ።

ተመላሾቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄነራል ተወካይ አቀባበል ማድረጋቸውን ከሚኒስቴሩ ቃልአቀባይ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።