ከሳዑዲ አረቢያ 1 ሺህ 657 ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

ሰኔ 23/2013 (ዋልታ) – ከሳዑዲ አረቢያ በትናትናው ዕለት 1 ሺህ 657 ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ የተቀናጀ ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል፡፡