ከተማ አስተዳደሩ ከ194 ሺሕ በላይ ዜጎች የማዕድ ማጋራት እያካሄደ ነው

የማዕድ ማጋራት

ሚያዝያ 13/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ194 ሺሕ በላይ ምንም ገቢ ለሌላቸውና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ዜጎች የማዕድ ማጋራት መርኃግብር እያካሄደ ነው።

የማዕድ ማጋራቱ በከተማ ደረጃ በ11 ክፍለ ከተሞች፣ በ120 ወረዳዎች እንዲሁም በ6 ሺሕ 885 ብሎኮች በተመሳሳይ እንደሚካሄድ ተገልጿል።

ከተማ አስተዳደሩ በኑሮ ውድነቱ ጫናና ተደራራቢ በዓልን ምክንያት በማድረግ ገቢ ለሌላቸውና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ዜጎች ነው መዓዱን እያጋራ የሚገኘው።

በዙፋን አምባቸው

 

ለፈጣን መረጃዎች፦

ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW

ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth

ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

ቲዊተር https://twitter.com/walta_info

አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!