ከንቲባዋ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦርድና ስራ አስፈፃሚ አመራር አባላት ጋር ተወያዩ

ኅዳር 1/2015 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦርድና የስራ አስፈፃሚ አመራር አባላት ጋር በትብብርና በጋራ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡

በዚህም በቤቶች ልማትና በሌሎች የልማት ስራዎች ላይ በጋራ ለመስራት ምክክር መደረጉን ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦርድና የስራ አስፈፃሚ አባላቱ በዘመናዊ መልክ ታሪካዊ ይዘቱን ሳይለቅ የታደሰውን የማዘጋጃ ቤት ህንፃ እድሳት የጎበኙ ሲሆን በእድሳቱ ስራና በተመለከቱት ለውጥ መደሰታቸውን ገልጸዋል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW