ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለኢድ- አልፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

ሚያዝያ 23/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለኢድ- አልፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡

የአንድ ወር የረመዳን የጾም ወቅት የመረዳዳት፣ የመተሳሰብ እና የአብሮነት እንደነበር ገልጸዋል፡፡

ከንቲባዋ ቀጣዩም ጊዜ ይህንኑ መረዳዳት እና አብሮነት በማጠናከር ሰላማችንን ዘላቂ የምናደርግበት ይሁን ሲሉ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡