ከንቲባ ፀጋዬ ቱኬ በዓልን ሆስፒታል ከሚገኙ ህሙማን ጋር አከበሩ

መስከረም 1/2015 (ዋልታ) የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፀጋዬ ቱኬ የአዲስ ዓመት በዓልን በከተማዋ ሪፈራል ሆስፒታል ከሚገኙ ህሙማን ጋር አክብረዋል።
ከንቲባው በሆስፒታሉ ለሚገኙ ህሙማን የምሳ ግብዣ በማድረግም ማዕድ አጋርተዋል።
ከንቲባው በዚህ ወቅት በሆስፒታል ከሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር በዓላትን ማክበር ልዩ ትርጉም የሚሰጠው ነው ብለዋል።
ሁሉም ሰው በተለይም በበዓል ወቅት እነዚህን ወገኖችን በማስታወስ በጋራ ማክበርን መልመድ ይገባዋል ማለታቸውን የከተማው ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መረጃ አመላክቷል።
በሆስፒታሉ የሚገኙ ህሙማን በበኩላቸው ዛሬ በተደረገላቸው ጉብኝትና የምሳ ግብዣ መደሰታቸውን ገልጸዋል።