ከአልኮል ነፃ ቀን በስፖርታዊ እንቅስቃሴ እየተከበረ ነው

የካቲት 27/2014 (ዋልታ) ከአልኮል ነፃ ቀን በኢትዮጵያ ዛሬ በስፖርታዊ እንቅስቃሴ እየተከበረ ይገኛል።

ከአልኮል ፍሪ ጀነሬሽን ኢትዮጵያ ድርጅት ባዘጋጀው በዚህ ፕሮግራም የ5 ኪሎ ሜትር የሩጫና የእግር ጉዞ እየተካሄደ ነው።

መነሻና መድረሻውን ቦሌ አትላስ ባደረገው በዚህ ውድድር በርካታ ሰዎች ተሳትፈዋል።

ከአልኮል ነፃ ትውልድን በኢትዮጵያ በመፍጠር ለአገር እድገትና ኢኮኖሚ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያደርግ ትውልድ መገንባት ዋነኛ የድርጅቱ አላማ ነውም ተብሏል።
በሐብታሙ ገደቤ