ከኢትዮጵያ ተሰርቀው የወጡ 13 የተለያዩ ቅርሶች ተመለሱ

ኅዳር 11/2014 (ዋልታ) በመቅደላ ጦርነት ወቅት ከኢትዮጵያ ተሰርቀው የወጡ አስራ ሶስት የተለያዩ ቅርሶች ተመለሱ፡፡

የቱሪዝም ሚኒስትሯ አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ቅርሶቹን ለማስመለስ ከፍተኛ ጥረት ሲደረግ መቆየቱን ገልጸዋል፡፡

የእጅ መስቀል፣ ዘውድ፣ የጸሎት መጽሐፍት፣ መጠጫዎች እና የተለያዩ ሃይማኖታዊ ቅርሶች ከተመለሱት መካከል ተጠቃሾች ናቸው፡፡

ቅርሶቹን ለማስመለስ በእንግሊዝ የኢትዮጵያ ኢምባሲ፣ በእንግሊዝ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም ቅርስ አስመላሽ ኮሚቴ ከፍተኛ ጥረት ማድረጋቸውን ሚኒስትሯ ተናግረዋል፡፡

ኢዜአ እንደዘገበው ቅርሶቹ በአግባቡ ተጠብቀው ለጎብኝዎች ክፍት እንዲሆኑ ከማድረግ ባሻገር ለጥናትና ምርምር ከፍተኛ ፋይዳ እንዳላቸውም ተጠቁሟል፡፡