ከኤሌክትሪክና ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ወጪ ንግድ 24 ሚሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱ ተገለጸ

ሐምሌ 27/2017 (ዋልታ) – በ2013 በጀት ዓመት ወደ ውጪ ከተላከ የኤሌክትሪክ፣ ኤሌክትሮኒክስና ኮሙዩኒኬሽን ዕቃዎች 24 ሚሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ገቢው የተገኘው ወደ ተለያዩ ሀገራት ከተላኩ የኤሌክትሪክ፣ ኤሌክትሮኒክስና ኮሙዩኒኬሽን ምርቶች ሲሆን 80 በመቶ የሚሆነውን ገቢ ያስገኘው የትራንሺ (ቴክኖ) ምርት መሆኑ ነው የተገለፀው፡፡

ከዘርፉ 41 ሚሊየን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ የእቅዱን 58 ነጥብ 5 በመቶ ገቢ መገኘቱን ከንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በሌላ በኩል  15 አዳዲስ ፋብሪካዎች ወደ ስራ መግባታቸውንና ለ1ሺህ  500 ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር  መቻሉን የኤሌክትሮኒክስ፣ ኤሌክትሪክና ኢንፎርሜሽ ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ኢንዱስትሪ ጥናት ክትትልና ድጋፍ ዳይሬክተር አቶ ፀሐዬ ይነሱ ተናግረዋለ፡፡