ከውጪ የገባው የምግብ ዘይት ለክልሎች መከፋፈል

ጳጉሜ 5/2013 (ዋልታ) የዘመን መለዋጫ በዓልን አስመልክቶ የዘይት አቅርቦት ችግር እንዳይከሰት ከውጪ የገባው የምግብ ዘይት ወደ ክልሎች እየተከፋፈል መሆኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በሚኒስቴሩ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አበባ ታመነ እንደገለፁት መንግስት በሃገሪቱ በአሁኑ ወቅት በተከሰተው ጦርነት ምክንያት በርካታ ጫናዎች ቢኖሩበትም ጫናውን ተቋቁሞ ሃገር እንድትቀጥል ጥረቶች በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

መንግስት የዘመን መለወጫ በዓል መምጣቱን ተከትሎ ህብረተሰቡ የዘይት አቅርቦት ችግር እንዳይገጥመው በማሰብ ያለውን ውስን የውጪ ምንዛሬ ተጠቅሞ ዘይት ከውጪ ሃገር ማስመጣቱን ዳይሬክተሯ ተናግረዋል፡፡

ስለሆነም በአሁኑ ወቅት ከውጪ የገባው ዘይት በአንዳንድ ምክንያቶች በተፈለገው ጊዜ ባይደርስም፣ አሁን ግን ለክልሎች እየተሰራጨ እንደሚገኝ መግለጻቸውን ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡