ከ135 ሺሕ በላይ ሜትሪክ ቶን የምግብ ነክ ድጋፍ ለትግራይ ክልል መደረጉ ተገለጸ

ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ

ሰኔ 16/2014 (ዋልታ) ባለፈው አንድ ዓመት ከ135 ሺሕ በላይ ሜትሪክ ቶን የምግብ ነክ ድጋፍ ለትግራይ ክልል መደረጉ ተገለጸ።

የብሔራዊ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ ለትግራይ ክልል እየቀረበ ያለውን ድጋፍ በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸው በክልሉ 5 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዜጎች ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን ገልጸው እየተደረገ ያለው ድጋፍ ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ድጋፎች፣ ጥሬ ገንዘብ፣ የህክምና መሳረያዎች እንዲሁም ነዳጅን ያካተተ ነው ብለዋል።

ይህንን ድጋፍ ለማሳለጥ እንዲቻል በቀን ከ300 በላይ መኪኖች በአሁኑ ጊዜ ወደ ከልሉ እርዳታ በማድረስ ላይ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

በተጨማሪም ኮሚሽነሩ በመግለጫቸው 19 ነጥብ 1 ሚሊዮን ኩንታል የዕለት ደራሽ እርዳታ በድርቅ ለተጎዶ ክልሎች ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን አመላክተዋል።

በዚህም ድጋፍ ከ540 ሺሕ በላይ ሜትሪክ ቶን የምግብ እርዳታ የተደረገ ስለመሆኑ አንስተዋል።

ከክረምቱ መምጣት ጋር በተያያዘ ለሚከሰቱ የጎርፍ አደጋዎች የቅድመ መከላከል ሥራዎችን ከክልሎች ጋር በመቀናጀት እየተሰራ ስለመሆኑም ገልጸዋል።

በሰለሞን በየነ

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW