ከ2 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የኮንትሮባንድ እቃ ተያዘ

የኮንትሮባንድ እቃ

ግንቦት 13/2014 (ዋልታ) በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ጎሮ ጉቱ ወረዳ በሮዳ ከተማ ከሁለት ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃ በቁጥጥር ስር መዋሉን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።

የዞኑ ኮሙዩኒኬሽንና ሚዲያ ድቭዥን ኃላፊ ዋና ኢንስፔክር ቶሎሣ ጎሹ እንደገለፁት ኮድ 3 የሰሌዳ ቁጥር 72792/ኦሮ የጭነት ተሽከርካሪ 2 ሚሊየን 172 ብር የሚገመት የኮንትሮባንድ እቃ ጭኖ ወደ ምዕራብ ሀረርጌ ሊያልፍ ሲል በሮዳ ከተማ ላይ በቁጥጥር ስር ውሏል።

በቁጥጥር ስር የዋለው የኮንትሮባንድ እቃም ሲጋራ መሆኑን ጠቆሙት ኃላፊው የኮንትሮባንድ እቃው ከነ ተሽከርካሪው በቁጥጥር ስር የዋለ ቢሆንም አሽከርካሪው ለጊዜው መሰወሩንና ክትትል እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

ኅብረተሰቡም ኮንትሮባንድን ከመከላከል አንፃር እያደረገ የሚገኘውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

ተስፋዬ ኃይሉ (ከሀረር)

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW