ከ5 ሺሕ በላይ የክላሽ ጥይት ወደ አዲስ አበባ ለማስገባት የሞከሩ ሶስት የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ጥር 19/2014 (ዋልታ) ከ5 ሺሕ በላይ የክላሽ ጥይት ወደ አዲስ አበባ ለማስገባት የሞከሩ ሶስት የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

ሶስቱ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪዎች ከባሕርዳር ወደ አዲስ አበባ በቁጥር 5,610 የሚሆን የክላሽ ጥይት ወደ አዲስ አበባ ከተማ እንዲገባ በማድረግ ለሽያጭ  ሊያቀርቡ ሲሉ በተደረገ ክትትል በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

ጥይቱን  በአይሱዙ  ተሽከርካሪ ውስጥ ሻግ በመስራትና በውስጡ በማድረግ ለሽያጭ ሊያቀርቡ እንደነበርም ታውቋል፡፡

ሆኖም   የጦር መሳሪያውን (ጥይቱን) ጨምሮ  3ቱም አዘዋዋሪዎች ከፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል።