ከ650 በላይ ከስደት ተመላሽ ዜጎች በተለያዩ የሙያ መስኮች ተመረቁ

ሰኔ 08/ 2013(ዋልታ) – የአዲስ አበባ ከተማ ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ከከተማ አስተዳደሩ ቴክኒክና ሙያ ኤጀንሲ ጋር በመተባበር ለአራተኛ ዙር ነው ከስደት ተመላሾችን አሰልጥኖ ያስመረቀው።

በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥረር አባይን ጨምሮ በርካታ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች መሳተፋቸውን ከአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

በስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር ዓባይ ተመራቂዎቹ የከተማ አስተዳደሩ ድጋፍ ሳይለያቸው በሀገር ሰርቶ መለወጥ እንደሚቻል ምሳሌ ይሆናሉ ብለዋል፡፡

ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን ከመሰረቱ ለመከላከል የዜጎችን  ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ ችግርችን መቅረፍ ይገባልም ነው ያሉት፡፡

ዜጋ ተኮር ፖሊሲ የመንግሥት ግልፅ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ በመሆኑ በውጭ የሚኖሩ ዜጎቻችን ተገቢውን ክብር አንዲያገኙ እየተሰራ ነው ብለዋል።

የዜጎች ሰብዓዊ መብት እንዲከበር ከመስራት ባሻገር በአገር ውስጥ የስራ እድል በማስፋት ዜጎችን ተጠቃሚ የምያደርግ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።