ከ82 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

መጋቢት 17/2014 (ዋልታ) ባሳለፍነው ሳምንት ከ82 ሚሊየን 714 ሺሕ ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የገቢና የወጪ የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸውን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
ኮሚሽኑ ባሳለፍነው ሳምንት ባደረገው ክትትል 76 ሚሊየን 535 ሺሕ ብር የገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎች እና 6 ሚሊየን 178 ሺሕ ብር የሚያወጡ የወጪ የኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ተይዘዋል፡፡
የገቢ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር ረገድ ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዙት ሞያሌ፣ ድሬዳዋ እና ጅግጅጋ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ሲሆኑ በቅደም ተከተላቸው 22.6 ሚሊየን፣ 21.9 ሚሊየን እና 8 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዝ ችለዋል፡፡
በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ ነዳጅ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድኃኒት ፣ ተሽከርካሪዎች፣ የመዋቢያ እቃዎች የጦር መሳሪያዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች የግንባታ ብረት እና የተለያዩ አገራት ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡
የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች፣ በፌዴራል ፖሊስ፣ በክልል ፖሊስ አባላትና ኅብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻ፣ በበረራና በጥቆማ መያዛቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡