ኪር ስታመር የዩኬ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ

ኪር ስታመር

ሰኔ 28/2016 (አዲስ ዋልታ) በብሪታንያ ትናንት በተካሄደው ጠቅላላ ምርጫ አብላጫውን ድምጽ በማግኘት ያሸነፈው የሌበር ፓርቲ መሪ ኪር ስታመር ከንጉስ ቻርለስ ጋር በቤኪንግሃም ቤተመንግስት ከተገናኙ በኋላ በይፋ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል፡፡

ፓርቲያቸው ከአጠቃላይ ከ650 የምክር ቤት ወንበር 411 ያህሉን በመያዝ ጠቅላላ ምርጫውን ማሸነፉ የሚታወስ ነው፡፡

የወግ አጥባቂው ፓርቲ በበኩሉ 144 ወንበር እንዳገኘ የተገለጸ ሲሆን ይህም በታሪኩ አነስተኛው ነው ተብሏል።

አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኪር ስታመር ፓርቲያቸው በምርጫው በማሸነፉ ለደጋፊዎቻቸው አሳካነው ሲሉ የደስታ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

ከ14 ዓመታት በኋላ ወግ አጥባቂውን ፓርቲ የሚተካው የሌበር ፓርቲው መሪ ኪር ስታመር ዛሬ ከሪሺ ሱናክ ጋር የስልጣን ርክክብ አድርገዋል፡፡

የተለያዩ አገራት መሪዎችም ለኪር ስታመር የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡