ኮሚሽኑ የሦስት ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ ላይ የባለድርሻ አካላት ምክክር እያካሄደ ነው

ሐምሌ 23/2014 (ዋልታ) ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የሦስት ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ ላይ የባለድርሻ አካላት ምክክር እያካሄደ ነው።
በኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዩች ምክር ቤት በአዋጅ ቁጥር 1265/2014 የተቋቋመው ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በሀገሪቱ የተፈጠሩ ፖለቲካዊ አለመግባባቶችን በጥናትና በሕዝባዊ ውይይቶች በመለየት ሀገራዊ ምክክሮችን በማካሄድ ለሀገራዊ መግባባት ምቹ ሁኔታዎችን የመፍጠር ተልእኮ ተሰጥቶታል።
ኮሚሽኑ ችግሮችን ለይቶ የምክክር መድረኮችን በመፍጠር ሀገራዊ የፖለቲካ አለመግባባቶችን ለመፍታት የ3 ዓመት የጊዜ ገደብም ተሰጥቶታል።
በእነዚህ ሦስት ዓመታት የሚከናወኑ ተግባራትን በተመለከተ ኮሚሽኑ ስትራቴጂክ እቅድ አዘጋጅቶ ወደ ሥራ ገብቷል።
በዛሬው እለትም በስትራቴጂክ እቅዱ ዙሪያ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ውይይት እየተካሄደ ነው።
በዚህ የውይይት መድረክ እቅዱን ለማዳበር የሚያስችሉ ሀሳቦች ይነሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በጌታቸው መኮንን