ነሐሴ 26/2013 (ዋልታ) – ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር 4 ሚሊየን 289 ሺህ ብር እንዲሁም የቀ.ኃ.ሥ ሐረር የጦር አካዳሚ አልሙናይ ማህበር 367 ሺህ ብር ድጋፍ ድጋፍ ለመከላከያ ሰራዊት አደረገ።
116 የሚሆኑ የኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግል ማህበር ሰራተኞች የአንድ ወር ደመወዛቸውን ከመስጠት ባለፈ ደሜን ለሀገሬ ደሜን ለመከላከያ በሚል ደም እንደሚሰጡም ተገልጿል።
107 የሚሆኑ የማህበሩ ሰራተኞች የቀድሞ የፖሊስ እና መከላከያ ሰራዊት አባላት የነበሩ ሲሆን፣ ወደ ግንባር በመሄድ ሀገር የማዳን ተልዕኮ እየተወጡ መሆኑን የማህበሩ ዳይሬክተር ጀነራል ኮማንደር ጥላሁን ፀጋዬ ተናግረዋል።
የቀ.ኃ.ሥ ሐረር የጦር አካዳሚ አልሙናይ ማህበር ምክትል ፕሬዝዳንት ሻምበል በቀለ ፀጋዬ በበኩላቸው፣ ለሰራዊቱ ከገንዘብ ድጋፉ ባለፈ በሙያ እና በዓይነት የሚቻለውን ሁሉ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ነን ብለዋል።
የመከላከያ ሚኒስቴር የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ ብርጋዴር ጄነራል አስረስ አያለው ለተደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
(በትዕግስት ዘላለም)