ወሎ ዩኒቨርሲቲ ያሰለጠናቸውን 823 ተማሪዎች አስመረቀ

ግንቦት 14/2014 (ዋልታ) ወሎ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 823 ተማሪዎች አስመረቀ፡፡

የዩኒቨርሲቲው የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ብርሃኑ አሰፋ (ዶ/ር) እንደገለፁት ከተመራቂዎች መካከል 293ቱ ሴቶች ናቸው።

ዩኒቨርሲቲው በአሸባሪው ህወሓት ከወደመ በኋላ በቅንጅት መልሶ ተቋቁሞ የመማር ማስተማር ስራውን ዳግም በመጀመር ነው ለዚህ የደረሰው ብለዋል፡፡

ተመራቂዎቹ የሽብር ቡድኑ በፈጸመው ወረራ ትምህርታቸው ቢስተጎጎልም ቅዳሜና እሁድ ጭምር አካክሰው ቆይታቸውን ያጠናቀቁ መሆናቸውን ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡

ከተመረቁት ውስጥ 106ቱ በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን የተከታተሉ መሆኑን መሆናቸውን የዩኒቨርሲቲው መረጃ አመላክቷል፡፡