ወታደራዊ ስልጠና ሳይሰጠን ወደ ጦርነት ገብተናል – የትግራይ ተወላጆች

ነሐሴ 23/2013 (ዋልታ) – ምንም አይነት ወታደራዊ ስልጠና ሳይሰጠን የትህነግን ቁስለኛና ተተኳሽ ጥይቶች እንድናመላልስ ከያለንበት ታፍሰን ወደ ጦርነት እንድንገባ ተደርገናል ሲሉ እጃቸውን በማይጠብሪ ግንባር ለሚገኘው ሰራዊት የሰጡ የትግራይ ተወላጆች ገለፁ።

ከእንዳባጉና እና ከሽሬ አዲአሮ አካባቢ ትህነግን እንዲቀላቀሉ የተደረጉት ጎይቶም ሃዱሽ  እና  ግርማይ ቴወድሮስ ሌሎች በርካታ ቁጥር ያላቸው ወጣቶች እንደነሱ ሽብርተኛ ቡድኑን ትተው በተለያዩ ቦታዎች እንደተበተኑ ተናግረዋል።

ወጣቶቹ ትግራይ ስላለው ሁኔታ ሲገልጹ ከእያንዳንዱ የቤተሰብ ቁጥር ግማሽ ያህሉ ወደ ጦርነት እንዲገባ ትህነግ ባስቀመጣቸው የየአካባቢው ሹመኞች ይገደዳል።

ለእርዳታ እንዲመዘገብ የሚጠየቅ ቤተሰብ ቁጥሩን በዕጥፍ እንዲያደርግና ግማሹን ለትህነግ ሰራዊት እንዲሰጥ ይደረጋልም ብለዋል።

የትግራይ ነዋሪ በአሁኑ ሰአት ጥያቄ እያነሳ መሆኑንም አክለዋል ።

ወጣቶቹ በነበሩበት የጦር ሜዳ ቆይታም አንድ ብስኩት ለአንድ ቀን ይሰጣቸው እንደነበር  ገልጸዋል።

(በታሪኳ መንግስተአብ)