የሰብአዊ እርዳታ የጫኑ ተጨማሪ 85 ተሽከርካሪዎች መቀሌ መድረሳቸው ተገለጸ

ግንቦት 8/2014 (ዋልታ) የዓለም ምግብ ፕሮግራም 85 የሰብአዊ አርዳታ የጫኑ ተስከርካሪዎች ትላንት መቀሌ መድረሳቸውንና ተጨማሪ 130 የሰብአዊ እርዳታ የጫኑ ተስከርካሪዎች ወደ ትግራይ እየተጓዙ መሆናቸውን አስታወቀ፡፡
ወደ ትግራይ ክልል የሚላከው የሰብአዊ እርዳታ ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠሉን የገለጸው የዓለም ምግብ ፕሮግራም የሰብአዊ እርዳታ የጫኑ ከባባድ ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይና አፋር ክልል እየገቡ መሆናቸውንና ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው አካላት የማዳረስ ሥራ እየተሰራ መሆኑን አመልክቷል፡፡
ወደ አፋር እየተጓጓዘ የሚገኘው እርዳታ ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን በቀጣዮቹ ቀናትም እስከ 36 ሺሕ ለሚደርሱ ሰዎች ድጋፉን ለማዳረስ እየተሰራ መሆኑ ተነግሯል፡፡
የዓለም ምግብ ፕሮግራም – ኢትዮጵያ በትዊተር ገጹ ባሰፈረው መልዕክት በዚህ ዙር የተጓዘው የሰብአዊ እርዳታ ከዚህ ቀደም ከተላኩት በአይነቱ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁሟል፡፡

ይሁን እንጂ የተባበሩት መንግስታት የምግብ ፕሮግራም እስካሁን ወደ ትግራይ እየተጓጓዙ ስላሉት የሰብዓዊ እርዳታ መጠን ያለው ነገር የለም፡፡

በነስረዲን ኑሩ