ወደ ጎንደር እና ባሕር ዳር የበረራ መስተጓጎል ማጋጠሙ ተገለፀ

ጥር 29/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ጎንደር እና ባሕር ዳር የበረራ መስተጓጎል እንዳጋጠመው አስታወቀ፡፡
አየር መንገዱ በጎንደር እና በባህር ዳር ከተሞች በተፈጠረ አስቸጋሪ የአየር ጠባይ ለውጥ ምክንያት የበረራ መስተጓጎል እንዳጋጠመው ነው ያሳወቀው፡፡
ለተፈጠረው መጉላላት ይቅርታ የጠየቀው አየር መንገዱ ሁኔታውን በተመለከተ ለደንበኞቹ ወቅታዊ መረጃዎችን እንደሚያደርስ በማኅበራዊ ትስስር ገጾቹ ይፋ ጠቁሟል፡፡