ወ/ሮ አዳነች አቤቤ 3ኛውን የምገባ ማዕከል አስጀመሩ

ግንቦት 05/2013 (ዋልታ) – ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በአዲስ ከተማ የተገነባውን 3ኛ ተስፋ ብርሀን አሙዲን የምገባ ማዕከልን መርቀው በይፋ የምገባ አገልግሎት አስጀመሩ።
የከተማ አስተዳደሩ ከሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ እና ዳሽን ባንከ ጋር በመተባበር ሦስተኛውን ተስፋ ብርሀን አሙዲን የምገባ ማዕከል በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አሜሪካን ጊቢ አካባቢ ተመርቆ በይፋ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል ።
እያንዳንዱን የከተማችን ነዋሪዎች በፍትሃዊነት ማገልገል ቀዳሚ መርሃችን ነው ያሉት ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ዛሬ ተመርቆ ስራ የጀመረው የተስፋ ብርሃን አሙዲ የምገባ ማእከል በርካታ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን በቀን አንድ ጊዜ መመገብ የማይችሉትን ለመመገብና የክህሎት ስልጠና የሚሰጥበት ነው ብለዋል።
የከተማችን በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ያሉትን መደገፍ የመንግስት ብቻ ሳይሆን የሁሉም ኢትዮጵያዊ ሃላፊነት መሆንን ገልጸዋል ።
ኢትዮጵያ የበርካታ የደጋጎች ሀገር ናት ፣ይህ የተስፋ ብርሃን አሙዲ ምገባ ማእከል እውን እንዲሆን ከሩቅም ሆነው ድጋፍ ላደረጉት ሼህ መሀመድ አሊ አላሙዲን፣ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ፣ ዳሽን ባንክ፣ የቢል ኤንድ ሚሊንዳጌትስ ፋውንዴሽን ላደረጉት አስተዋጽኦ በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋና አቅርበዋል።
የተስፋ ብርሀን አሙዲን የምገባ ማዕከል በቀን አንድ ጊዜ መመገብ ለማይችሉ ከ2ሺህ በላይ ነዋሪዎች የምገባ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል እንደሆነ ተገልጿል።
(ምንጭ ፡-አዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪ)
<img class=”j1lvzwm4″ src=”data:;base64, ” width=”18″ height=”18″ />