ዋልታ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ

መስከረም 28/2014 (ዋልታ) ዋልታ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬት አ.ማ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል የስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ።

ሁለቱ ተቋማት 10 አመት የዘለቀ የስራ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን፣ የኢትዮጵያ የጥራት ድርጅት በመመስረት ጥራትን በማስተዋወቅ ረገድ በርካታ ስራዎችን እየሰሩ ይገኛሉ።

የዋልታ ሚዲያና ኮርፖሬሽን ኮርፖሬት ዋና ስራ አስፈጻሚ ንጉሴ መሸሻ (ዶ/ር) ዋልታ የሳይንስ፣ የፈጠራና የምርምር ቲቪ ቻናል ለመጀመር እቅድ እንዳለው አንስተው፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በተለይ በምርምሩ መስክ በርካታ ስራዎች በጋራ እንሰራለን ብለዋል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጣሰው ወልደሃና (ፕሮፌሰር) በበኩላቸው፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከአፍሪካ ቀዳሚ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል አንዱ መሆኑን ገልጸው፣ ዩኒቨርሲቲውን የሚያስተዋውቅ ስራዎችን ከዋልታ ጋር ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት አመልክተዋል።

ተቋማቱ ለሁለት ዓመት የሚቆይ ስምምነት ነው የተፈራረሙት።

በመስከረም ቸርነት