ዓለም ዐቀፍ የሴቶች ቀን በመከላከያ መኮንኖች ክበብ እየተከበረ ነው

ዓለም ዐቀፍ የሴቶች ቀን

የካቲት 29/2014 (ዋልታ) ዓለም ዐቀፍ ተሴቶች ቀን (ማርች ኤይት) በተለያዩ ዝግጅቶች በመከላከያ መኮንኖች ክበብ እየተከበረ ነው።

በዓለም ዐቀፍ ደረጃ ለ111ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ46ኛ ጊዜ በሚከበረው የሴቶች ቀን የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና የሰራዊቱ አመራሮች ተገኝተዋል።

ቀኑ በአገር ዐቀፍ ደረጃ “እኔም የእህቴ ጠባቂ ነኝ!!” በመከላከያ ደግሞ “የአገራችን ሰላም በሴቷ ተጋድሎ ህያውነት ይረጋገጣል” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ መሆኑን ከመከላከያ ሰራዊት የተገኘው መረጃ አመላክቷል።

የመከላከያ ሴቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ባዘጋጀው የማርች 8 አከባበር ላይ የፓናል ውይይትና የመፅሐፍ ምረቃ ይካሄዳል ተብሎም ይጠበቃል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW