የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ለሴቶች አደረገ

መስከረም 28/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በሱሉልታ ከተማ ለሚኖሩ አቅመ ደካማ ሴቶች ድጋፍ አደረገ።
የጉባኤው ጠቅላይ ጸሐፊ ቀሲስ ታጋይ ታደለ በሱሉልታ ከተማ በመገኘት ድጋፉን አስረክበዋል።
ጉባኤው ድጋፉን ያደረገው ከኖርዌይ ቤተክርስቲያን ጋር በመተባበር መሆኑን ጠቅሰው፤ ድጋፉም በዋናነት የሴቶች ንጽሕና መጠበቂያ፣ ሳሙና እና ሳኒታይዘር ያካተተ መሆኑን ተናግረዋል።
ወቅቱ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ እየተስፋፋ ያለበት በመሆኑ በሽታውን ለመከላከልና በዋናነትም ሴቶችን ለማገዝ ያለመ ድጋፍ መሆኑን ለኢዜአ ተናግረዋል።
እርዳታው የሴቶችን ችግር በማቃለል ረገድ በጎ ሚና እንዳለው መናገራቸውን ድጋፉን የተረከቡት የተፈናቃዮቹ ተወካይ ወይዘሮ ፀሐይ ጌታሁን ተናግረዋል፡፡
ጉባኤው ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበው፤ ሌሎች ተቋማትም የጉባኤውን አርአያነት በመከተል ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!