የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የሰብዓዊ ድጋፍ ዘመቻ አስጀመረ

መስከረም 20/2014 (ዋልታ) – “የላቀ በጎነት እና ሰብዓዊነት ለሀገር ሰላም” በሚል መሪ ሃሳብ በሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂዎች ለሰብዓዊ ድጋፍ ዘመቻ ተጀመረ፡፡

ዘመቻው በ2013 ዓ.ም በሰው ሰራሽ እና በተፈጥሮ አደጋ የተጎዱ እና የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር መበራከቱን ተከትሎ የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ ለማሰባሰብ ያለመ ነው ተብሏል፡፡

ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የተጀመረው ዘመቻ በኢትዮጰያ ንግድ ባንክ የባንክ አካውንት 1000430591251 እና የዶላር አካውንት 0100051300080 ተከፍቷል፡፡

በዚህም ሁሉም ሰው የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል፡፡

በሜሮን መስፍን