የህልውና ዘመቻው በኬት እስኪጠናቀቅ የተጀመረው ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል- የጋምቤላ ክልላዊ መንግስት

ነሐሴ 07/2013(ዋልታ) – አሸባሪውን የህወሓት ቡድን ለመደምሰስ የተጀመረው የህልውና ዘመቻ በስኬት እስኪጠናቀቅ ድረስ የተጀመረው ሁለንተናዊ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የጋምቤላ ክልላዊ መንግስት ገለፀ።

የጋምቤላ ክልላዊ መንግስት ምክትል ርዕሰ መሰተዳድር አቶ ተንካይ ጆክ፤ የክልሉ ህዝብና መንግስት እስከ ወረዳ ያሉ አረደጃቶችን በመጠቀም ከ33 ሚሊዮን 500 ሺህ ብር ለማሰባሰብ አቅደው እየሰሩ እንደሚገኙ ለኢዜአ ተናግረዋል።

ከዚህም እስካሁን ከክልሉ ህዝብ በግንባር ለሚገኘው ሠራዊት ደጀንነቱን ለመግለጽ ከ15 ሚሊዮን 750 ሺህ ብር በላይ በጥሬ ገንዘብና ዓይነት ድጋፍ ተሰባስቧል።

አሁንም ከክልሉ የተጠናከረ የሰው ሃይል፣ የገንዘብ፣ ደምና የምግብ ነክ የቁሳቁስ ድጋፎች እየተሰባሰቡ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

በክልሉ እስከ ትናንት ባለው ጊዜ የእቅዱን ግማሽ ማሳካት መቻሉን ያመለከቱት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ፤ ከተሰበሰበው ገንዝብም ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ የጥሬ ገንዝብ፤ ቀሪው 750 ሺህ ብር ግምት ያላቸው ሰንጋ በሬዎችን ጨምሮ በዓይነት የተገኙ  የተለያዩ ምግብ ቁሳቁሶች እንደሆኑ አብራርተዋል።

ገንዘቡ የተሰበሰበው ከመንግስት አመራሮች፣ ሰራተኞች፣ ከንግዱ ማህበረሰብ፣ ከባለሃበቶችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ነው።

የክልሉ መንግስትና ህዝብ አሸባሪው ቡድን ሀገር ለማፍረስ የከፈተውን ጦርነት ለመቀልበስ የተጀመረው ዘመቻ በስኬት እስኪቋጭ ድጋፋቸው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ አስታውቀዋል።