የህክምና ቁሳቁስ የጫኑ የዓለም ዐቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ተሽከርካሪዎች መቀለ ገቡ

ሰኔ 24/2014 (ዋልታ) የህክምና ቁሳቁስ የጫኑ ተሽከርካሪዎች መቀለ መግባታቸውን በኢትዮጵያ የዓለም ዐቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ አስታወቀ፡፡

የህክምና ቁሳቁሶችን ጨምሮ የጤፍ ዘር እንዲሁም መሰረታዊ የቤት ቁሳቁሶችን ያካተተ ሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ዛሬ መቀሌ መግባታቸውን በኢትዮጵያ ከዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡