የህወሓት የሽብር ቡድን ታጣቂዎች ሰርገው በገቡባቸው አካባቢዎች እየተደመሰሱ ነው ተባለ


ነሐሴ 03/2013(ዋልታ) –
የህወሓት የሽብር ቡድን ታጣቂዎች ሰርገው በገቡባቸው አካባቢዎች እየተደመሰሱ መሆኑን የአማራ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ገለጸ፡፡
የኮሙዩኒኬሽኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ለኢብኮ እንደገለጹት የህወሓት የሽብር ቡድን ታጣቂዎች በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎችን በሃይል ወሯል፡፡
ሰርገው በገቡባቸው ቦታዎች ግድያ፣ ዘረፋ እና አስገድዶ መድፈር እየፈፀሙ መሆኑንም ጠቁመዋው የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች ሰርገው በገቡባቸው አካባቢዎች እየተደመሰሱ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡
የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች ሰርገው ከገቡበት አካባቢዎች ጠራርጎ ለማስወጣትና ለመደምሰስ ሁሉም የፀጥታ ሃይሎች በቂ የሥነ-ልቦና እና አካላዊ ዝግጅት ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡
የህወሓት የሽብር ቡድን ይህንን ቦታ ያዝን ያንን ቦታ ተቆጣጠርን እያለ በሚነዛው ፕሮፖጋንዳ ህብረተሰቡ ሳይደናገጥ ትክክለኛ መረጃን ከመንግስት አካላት ማግኘት እንዳለበት ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ህብረተሰቡ በተለይ ወጣቱ አካባቢውን በንቃት እና በትጋት በመከታተል እና በመደራጀት ለሰላሙ ዘብ ሊቆም ይገባል ማለታቸውን ኢብኮ ዘግቧል፡፡