የሆራ ሃርሰዴ የኢሬቻ በዓል በሰላም ተጠናቀቀ

መሰከረም 23/2014 (ዋልታ) የሆራ አርሰዴ ኢሬቻ በዓል ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ ተከብሮ በሰላም መጠናቀቁን የኦሮሚያ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ፡፡
ዓመታዊው የሆራ ሃርሰዴ የኢሬቻ በዓል ከሁሉም የኦሮሚያ ዞኖችና ከሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች የመጡ የተለያዩ የበዓሉ ታዳሚዎች በተገኙበት የበዓሉን ባህላዊ እሴት በጠበቀ መልኩ በቢሾፍቱ ከተማ ተከብሯል፡፡
ኢሬቻ የወንድማማችነት፣ የአንድነት እና የይቅርባይነት እሴቶችን ያየዘ ነው ያለው ቢሮው፣ ሆራ ፊንፊኔም ሆነ ሆራ አርሰዲ እነዚህኑ እሴቶ ባንፀባረቀ መልኩ በደመቀ ሁኔታ በሰላም ተከብሮ መጠናቀቁን ገልጿል።