የልደታ ክፍለ ከተማ አካባቢን የማፅዳት ሥራ አከናወነ

ታኅሣሥ 16/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የልደታ ክፍለ ከተማ “ውብ እና ፅዱ አዲስ አበባ” በሚል አካባቢን የማፅዳት ሥራ አከናውኗል።

ወደ አገር ቤት የሚመለሱ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ለመቀበል በሚደረገው ርብርብ ውስጥ ማኅበረሰቡ አካባቢውን ፅዱ በማድረግ ኃላፊነቱን ይወጣል ተብሏል።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር አባይ አዲስ አበባችንን ፅዱ እና ለነዋሪዎቿ ምቹ እንድትሆን በተጀመረው መርኃ ግብር ላይ የልደታ ክፍለ ከተማ የጀመረውን ንቅናቄ ሌሎች ክፍለ ከተሞችም ሊከተሉት ይገባል ብለዋል።

የፅዳት መርኃግብሩ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት በካርል አደባባይ አካባቢ ተከናውኗል።

በቁምነገር አሕመድ