የሎጂስቲክስ ወጪን ለመቀነስ በተከናወኑ ተግባራት 2 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ወጪ ማዳን መቻሉ ተገለጸ

ግንቦት 18/2014 (ዋልታ) የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ባለፉት 10 ወራት የሎጂስቲክስ ወጪን ለመቀነስ በተከናወኑ ተግባራት 2 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ወጪ ማዳን መቻሉን አስታወቀ፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ እያካሄደ ባለው 6ኛ ዙር 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባዔ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴርን የ2014 በጀት ዓመት የ10 ወራት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እያዳመጠ ይገኛል፡፡

ሪፖርቱን ያቀረቡት የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስ ባለፉት 10 ወራት የሎጂስቲክስ ወጪን ለመቀነስ በተከናወኑ ተግባራት 2 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ወጪ ማዳን መቻሉን አብራርተዋል።

በአጠቃላይ በቀረበው ሪፖርት መነሻነት የከተማ መሠረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አስተያየትና ጥያቄ እየቀረበ ሲሆን በሚኒስቴሩ የሥራ ኃላፊዎች ምላሽ እየተሰጠ መሆኑን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW