የመስቀል ደመራ በዓል አከባበር ዝግጅት

መስከረም 11/2014 (ዋልታ) መጪውን የመስቀል ደመራ በዓል በድምቀት ለማክበር ዝግጅት መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ ክስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት አስታወቀ፡፡

የቤተ ክህነቱ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሊቀ አዕላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን በበዓሉ አከባበር ቅድመ ዝግጅት ዙሪያ መግለጫ ስጥተዋል::

ምክትል ሥራ አስኪያጁ ባለፈው ዓመት በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት በጥቂት ሰዎች በዓሉ መከበሩን በመንሳት ዘንድሮ ተገቢውን የጥንቃቄ ተግባራት በመከወን በድምቀት ለማክበር መታሰቡን ገልጸዋል፡፡

የመስቀል ደመራ በዓሉ በድምቀት እንዲከበር በርካታ የቤተ ክርስቲያኗ ኮሚቴዎች እየተንቀሳቀሱ ነው ያሉት ምክትል ሥራ አስኪያጁ የበዓሉ ሥነ ሥርዓቶች እስከ ቀኑ 12 ሰዓት ድረስ ብቻ እንደሚከናወኑ ተናግረዋል፡፡

በዓሉ ያለምንም ፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!