የመከላከያ ሠራዊት ወታደራዊ ተንቀሳቃሽ ድልድይ ለማቅረብ እንቅስቃሴ መጀመሩን አስታወቀ

                              የመከላከያ ሠራዊት

ሰኔ 25/2013 (ዋልታ) – የመከላከያ ሠራዊት ወታደራዊ ተንቀሳቃሽ ድልድይ ለማቅረብ እና ለድልድዩም ጥበቃ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ አስታውቋል።

ሕወሃት የተከዜን ድልድይ ያወደመው የፌዴራል ሠራዊት እንዳይገባ ለማድረግ እንዲሁም የሰብዓዊ እርዳታ ሰጪዎች እርዳታውን በአውሮፕላን እንዲያደርሱ ለማድረግ መሆኑ ተገልጿል።

ሕወሃት የሰብዓዊ እርዳታ በአውሮፕላን የሚደርስ ከሆነ የእርዳታ ቁሳቁስ የጫኑ አውሮፕላኖች ላይ የሚደረገው ፍተሻ ይቀንሳል ብሎ እንደሚያምንም ተጠቁሟል።